የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት “ሩሲያ በዚህ ሳምንት ጥቃቷን ልታጠናክር ትችላች” ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 4 ወራትን ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀሩታል
ፕሬዝዳት ዘለንስኪ “ለሩሲያ ጥቃቶች እየተዘጋጀን ነው፤ ዝግጁ ነን” ሲሉ ተናግርዋል
የዩክሬኑ ፐሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ሩሲያ በያዝነው ሳምንት የምትሰንዝረውን ጥቃት ልታጠናክር ትችላች” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ከሆነ ሩሲያ የምትሰነዝረውን ጥቃት እንዲጨምር የሚያደርጋት ባሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ ላይ የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ዩክሬን የአውሮፓ ህብረትን እንድትቀላቀል ድጋፋቸውን በመግለጻቸው ምክንያት ነው።
ሞስኮ ዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት እንድትገባ መፍቀድን በመቃወም ተደጋጋሚ ዛቻዎችን ስታደርስ የቆየች ሲሆን፤ የምዕራባውያን መሪዎች ግን ዩክሬን ህብረቱን ለመቀላቀል ያቀረበችውን ጥያቄ በእጅጉ ደግፈዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ትናት ምሽት በሰጡት መግለጫ፤ “በዚህ ሳምንት እንደተለመደው ከሩሲያ የተጠናረ ጥቃት እንጠብቃለን” ብለዋል።
ከሩሲያ ለሚሰነዘርባው ማንኛውም ጥቃት እየተዘጋጁ እንደሆነ እና ዝግጁ እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን ባሳለፍነው ሳምንት ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት ለመቀላቀል ያቀረበችውን ማመልከቻ እንደማይቃወሙ ቢገልጹም፤ የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ምንያት የሚያደርገውን ተጽእኖ ግን ሞስኮ እንደማትታገስ አሳስበዋል።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩሲያ እና ዩክረን መካል የተጀመረው ጦርነት 4ኛ ወሩን ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀሩታል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሜር ዘሌንስኪ ከቀናት በፊት ባሰሙት ንግግር፤ በዩክሬን እየተካሄደ ያለው "ትርጉም-አልባ ጦርነት" እንዲያበቃ ምእራባውያን ከሩሲያ ጋር የገቡትን አላስፈላጊ ጨዋታ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።