ከ3 ለሚልቁ ወራት በህወሓት ቁጥጥር ስር የነበሩት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
የላሊበላ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በሌሎች የመንግሥት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ከ43 ዓመት በፊት ነበር በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው
ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት እንዳልደረሰበት የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ከ43 ዓመት በፊት ነበር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የሚዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት ከአንድ ዓመት በፊት በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ የቅርሱ ደህንነት ብዙዎችን አሳስቦ ነበር፡፡
ዩኔስኮም የፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ጉዳይ በጽኑ እንደሚያሳስበው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት የተናጠል የተኩስ አቁም መወሰኑን ተከትሎ በአማራ እና አፋር ክልሎች ጥቃት የከፈተው ህወሓት ካሳለፍነው ነሀሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ላሊበላ ከተማን ተቆጣጥሮ ቆይቶ ነበር፡፡
ይሁንና ከሰሞኑ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በወሰዱት መልሶ ማጥቃት አካባቢውን ከሶስት ከሚልቁ ወራት በኋላ መልሰው መቆጣጠራቸው አይዘነጋም፡፡
አል ዐይን ብዙዎችን አሳስቦ የቆየው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ቅርሶቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የደረሰባቸው ጉዳት አለወይ? ሲል የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንን ጠይቋል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ላሊበላ ከተማን ጨምሮ አካባቢው ከህወሃት ወረራ ነጻ መሆኑን ተከትሎ የቅርሱ ደህንነትን በተዘዋዋሪ ማጣራታቸውን ተናግረዋል፡፡
“እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስን ጨምሮ ሁሉም አገልጋይ መነኮሳት ጉዳት አልደረሰባቸውም” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብም በሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች እና አመራሮች ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ገልጸዋል፡፡
“አድዋ ላይ ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው ብቻ አይደለም የተዋጉት”
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል በበኩላቸው ሰሞኑን በተደረገው "ዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በዞኑ አምስት ወረዳዎችና ሶስት ከተማ አስተዳደሮች ከህወሃት ነፃ መውጣታቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በአካባቢው በቆየባቸው ጊዜያት የላሊበላ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያንና ሌሎች የመንግሥት ተቋማትን ጨምሮ የመሠረተ ልማት አውታሮችና የንግድ ተቋማትን ማውደማቸውንም ዋና አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል።