“ ‘ተማርኳል’ የሚለው መረጃ ምንጭ ራሴ ነኝ”-ሌ/ል ጄኔራል ባጫ ደበሌ
“የምንማረክ ከሆነ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው የሚሆነው” ሲሉም ተናግረዋል
“ባጫ ደበሌ ታንከኛ አይደለም ከታንክ ጋር የሚማርከው”ም ነው ጄነራሉ ያሉት
“ባጫ ደበሌ ታንከኛ አይደለም ከታንክ ጋር የሚማርከው”-ሌ/ል ጄኔራል ባጫ ደበሌ
ከ30 ታንክ ጋር ተማርከዋልመባሉን በማስመልከት በማዕከላዊ ትግራ ተራራማ ስፍራዎች ሆነው መግለጫ የሰጡት ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የመረጃው ምንጭ ራሴ ነኝ ብለዋል፡፡
“ጠላት ምን ሊያደርግ እንደሚችል እየተከታተልኩ ነው የማዋጋው ውጊያውን የምመራውም”ያሉት ጄነራሉ “መረጃውን የተናገረውንም ሰው አውቃለሁ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጠላትን ቡድን ማን እንደሚመራው እንደሚያውቁም ነው የገለጹት፡፡
“50 አለቃ ሆኖ ስመራው ነበር”ያሉም ሲሆን የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) “ሃገር እንዲያምስ ቀኝ እጅ ሆኖ” ሲያገለግል የነበረ እና አሁን የጄነራልነትን ማዕረግ ይዞ ሃገር የከዳ እንደሆነም ገልጸዋል እሳቸው በነበሩበት ግንባር የነበረ እንደሆነ በመጠቆም፡፡
“እግሬ አውጪኝ ብሎ ለራሱ እንዳይማረክ መግቢያ መውጫው የጠፋው ኃይል ባጫ ደበሌ የሚባለውን እንዴት አድርጎ ሊማርክ ይችላል?” ሲሉ የሚያጠይቁት ጄነራሉ “ባጫ ደበሌን ሊማርክ ቀርቶ በዓይኑ ሊያይ የማይችልበት ቦታ ላይ ነው ያለው” ሲሉ ይመልሳሉ፡፡
ከእሳቸው ፊት ያለው የሰራዊት ማዕበል “በእንዲህ ዓይነት የሚሊሻ ስብስብ ተሰብሮ መሪው የሚማረክበት ሁኔታ ላይ” እንዳይደለም ይገልጻሉ፡፡
መረጃው “በሬዲዮ መዋጋት ያቃተውን እምቢ ያላቸውን ሰራዊት ሞራሉን ለመገንባትና ለማነሳሳት ነው”ም ብለዋል፡፡
“ባጫ ደበሌ ታንከኛ አይደለም ከታንክ ጋር የሚማርከው”ም ነው ጄነራሉ ያሉት፡፡
ይህ መባሉ “አይደንቀኝም”ም ብለዋል፡፡
ይህን ለማድረግ “ማሰብ እና መመለስ”እንደሚጠይቅም ነው “ይኸው ዛሬም እየመራን ነው በማዕከላዊ ትግራይ ተራራዎች እንገኛለን” ያሉት ጄነራሉ የተናገሩት፡፡
“የምንማረክ ከሆነ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው የሚሆነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ቡድኑን “ካቴና አስገብተንለት ፍርድ ቤት ማቅረባችን የማይቀር”ም ነው ብለዋል፡፡
ጄነራል ባጫ ምናልባትም ነገ ወይ ከነገ ወዲያ ከጄነራል አበባው ታደሰ ጋር ሆነው በመቀሌ ጋዜጣዊ መግለጫን እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡