ፖለቲካ
መከላከያው በጊዜያዊነት ወደ ትግራይ ክልል አይገባም ተባለ
ውሳኔው መከላከያው በማንኛውም ቦታ ጊዜና ሁኔታ መግባት እንደሚችል በማሰብ መወሰኑም ነው የተነገረው
ጦሩ በያዛቸው ቦታዎች ጸንቶ እንደሚቆይ መንግስት አስታውቋል
የሃገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንደማይገባ መንግስት አስታወቀ፡፡
በክልሉ ይገኝ የነበረው ሰሜን እዝ ሲጠቃ ከክልሉ እንዳይወጣ ሲማጸን የነበረው ህዝብ መከላከል ቀርቶ አለማውገዙን የተናገሩት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጦሩ ከመግባት ይልቅ ነጻ አውጥቶ በያዛቸው ቦታዎች ጸንቶ እንዲቆይ ተወስኗል ብለዋል፡፡
ውሳኔው መከላከያው በማንኛውም ቦታ ጊዜና ሁኔታ ወደ ክልሉ መግባት እንደሚችል በማሰብ መወሰኑንም ነው ሚኒስትሩ የተነገሩት፡፡