ጄነራሉ “ከተማረክንም በህወሃት ጁንታ ሳይሆን በኢትዮጵውያን እና በኢትዮጵያዊነት ነው” ብለዋል
ተማርከዋል የተባለላቸው ሌተናል ጄኔራል ባጫ መግለጫ ሰጡ
ህወሓት ማርኬያቸዋለሁ ብሎ ያወራላቸው ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሃገር መከላከያ ሰራዊቱን ህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቅን አስመልክተው መግለጫ ሰጡ፡፡
ጄኔራል ባጫ በመግለጫቸው ህግ የማስከበሩ ዘመቻ ሶስተኛው ምዕራፍ ተጠናቆ ህዝብ በማረጋጋት ወደ ቀየው የመመለስ ተግባራት መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ቡድኑ በተለያዩ ከተሞች ሊፈፀማቸው የሚችሉ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶችን ለመከላከል ሰራዊቱ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝም ነው ጄኔራሉ ያስታወቁት።
“እየፈረጠጠ ያለ ቡድን ምንም አይነት የመማረክ አቅም ይኖረዋል” ያሉት ጄነራል ባጫ ተማርከዋል መባላቸውን በማስመልከት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስለ ጦርነት አውድ ያላቸው እውቀት አናሳነት ያሳያልም ነው ጄነራሉ ያሉት፡፡
“ጄነራሉ ከተማረክንም በህወሃት ጁንታ ሳይሆን በኢትዮጵውያን እና በኢትዮጵያዊነት ነው”ም ብለዋል እንደ ፋና ዘገባ፡፡
ዘመቻውን እና ቀጣይ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመሆን በመቀሌ መግለጫ እንደሚሰጡ ስለማስታወቃቸውም አብመድ ዘግቧል፡፡