በቀጣዮቹ 4 ዓመታት 70 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ መታወቂያን ይይዛሉ ተባለ
አዲስ አቅጣጫ ካልመጣ በስተቀር አሁን ያሉት መታወቂያዎች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል
“የብሔራዊ መታወቂያ ዓላማ የቀበሌ መታወቂያን መተካት አይደለም”- ዮዳሄ ዘሚካኤል፤ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ
ከ 10 ዓመት በፊት የተወጠነው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት አሁን በሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዋና ሥራ እንደሚገባ በተገለጸው በዚህ ፕሮጀክት በቀጣይ አራት ዓመታት ከ 70 ሚሊዮን የሚልቁ ኢትዮጵያውያ ብሔራዊ መታወቂያ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ ብሔራዊ መታወቂያ ሲባል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ዜጋም ሆነ ነዋሪ የትኛውንም አገልግሎት ሲያገኝ እራሱን የሚለይበት እና የሚያስተዋውቅበት መንገድ እንደሆነ የገለጹት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል መታወቂያውን በ2018 ዓ.ም ህፃናትን ሳይጨምር 95 ከመቶ ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ብሔራዊ መታወቂያ ማንኛውም ዜጋ ወይም ነዋሪ ሊኖረው የሚገባው መታወቂያ እንደሆነ ያነሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብሔራዊ መታወቂያ በካርድ ከሚሰጠው ይለያል ብለዋል፤ እኔነትን የሚያረጋግጥ የመረጃ ስርዓት እንደሆነ በመጠቆም፡፡
ራስን ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ማንኛውንም የመረጃ ስርዓት “ብሔራዊ መታወቂያ” ብሎ ጠቅለል አድርጎ መጥራት እንደሚቻልም አንስተዋል የፕሮጀክቱ ኃላፊ፡፡
በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን በላይ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ ተገለፀ
ብሔራዊ መታወቂያ በዋናነት ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር የመስራት ጉዳይ እንደሆነ ያነሱት አቶ ዮዳሄ፤ ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር በሚሰራበት ጊዜ፤ አንዳንዶቹ አገልግሎት ሰጭዎች መታወቂያ ማተም ሊፈልጉ እና አንዳንዶች ደግሞ በ“ዲጂታል ብቻ ይበቃናል” ሊሉ እንደሚችሉም አስታውሰዋል፡፡
እንደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ የመታወቂያ ካርድ የሚያትሙ አገልግሎት ሰጭዎች ላይ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እንደሚቀመጥም ነው የተገለጸው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተማሪዎች መስጠት የጀመረውን መታወቂያ እንደ አብነት ያነሱት ዋና ስራ አስኪጁ የብሔራዊ መታወቁያ ዓላማ የቀበሌ ወይም የነዋሪ መታወቂያን መተካት እንዳልሆነ አነስተዋል፡፡ ከዛ ይልቅ ብሔራዊ መታወቂያ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ማናቸውንም አገልግሎት ሰጭዎችን ማስተሳሰር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡
ጥንታዊው “የፓን አፍሪካኒዝም የጥበብ ት/ቤት በኢትዮጵያ”- አለፈለገ ሰላም
ለአብነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪነት መታወቂያ ሲሰጥ፤ ይህንን መታወቂያ ከሌሎቹ ጋር ማስተሳሰር የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ስራ እንደሆነም ተነስቷል፡፡
“አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል ስልት ባዮሜትሪክ የሚባል ዳታ፤ የእጅ እና የዐይን አሻራ፣ የፊት ፎቶ ከተያዝ በኋላ ብሔራዊ መታወቂያ ካዘጋጀው ልዩ ቁጥር ጋር እንደሚያያዝ ነው የገለጹት አቶ ዮዳሄ፡፡
ይህ ልዩ ቁጥር ከአሻራ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ የትኛውም አገልግሎት ሰጭ ጋር በመሄድ አገልግሎት ማግኘት ቢያስፈልግ፤ አገልግሎት ሰጭው የራሱን አገልግሎት ልዩ ቁጥር ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ያተሳስራል ተብሏል፡፡
አገልግሎት ሰጭው ከአንድ ዘርፍ ወደ ሌላ ዘርፍ ፤ከአንድ ሱቅ ወደሌላ ሱቅ፤ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ቢሄድም የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እንደማይቀየርና በዛ ቁጥር መሰረት እንደሚተሳሰር ተገልጿል፡፡
ለመልሶ ማቋቋም የ5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ
የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል ከአራት ዓመታት በኋላ በ2018 ዓ.ም 70 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዝ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርን በአካል በሚሰጥ እና መታወቂያ ላይ ያለውን መረጃ በመውሰድ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በያዝነው ዓመት “አነስ አነስ ያሉ የሙከራ ትግበራዎችን” ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር እንደሚሰራም ነው፤ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዋና ትግበራ ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡
ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር ፕሮጀክት በመቅረጽ እንደሚሰራ ያነሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ፤ ባንክ እንደምሳሌ ቢወሰድ ባንኩ አንድ የተለየ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኛው ወደ ባንኩ ቢሄድ ቅድሚያ “የብሔራዊ መታወቂያ አሻራህን ሰጥተህ ነው ይህንን አገልግሎት የምንሰጥህ እንዲል “የማስቻል ስራ ይሰራል ነው የተባለው፡፡ በዚህም መሰረት 10 ዲጂት ቁጥር ያለው የብሄራዊ መታወቂያ ቁጥር ከሌሎች ሴክተሮችም ጋር እየተሳሰረ እንደሚሄድ ተገልጿል፡፡
ብሔራዊ መታወቂያ የግድ በኪስ ተይዞ የሚኬድ እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ስራ አስኪጁ፤ ምናልባት የዛሬ አምስት ወይም 1 0 ዓመት ሁሉም መታወቂያዎች በብሔራዊ መታወቂያ ይቀየሩ ቢባል ካርዱን የማተም ሥራው አንድ በመቶ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
የሥራው 99 በመቶ ዳታውን መሰብሰብ እና ከዛ ከሲስተሞች ጋር ተናቦ ማረጋገጫ የመስጠት ሲሆን ካርድ መስጠት ግን እስካሁን በሕግ ደረጃ እንደሌለ ተገልጿል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ነዋሪነት ወይም አድራሻ የማረጋገጥ ስራ አይሰራም ብለዋል፡፡ አዲስ አቅጣጫ ካልመጣ በስተቀር አሁን ያሉት መታወቂያዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉና በነሱ ላይ የብሔራዊ መታወቂያ ልዩ ቁጥር እንደሚቀመጥ አስቀምጠዋል ስራ አስኪያጁ፡፡