በአማራ ክልል ተጥሎ ከነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ጋዜጠኞቹ ኢሰመኮን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ከእስር እንዲለቀቁ ሲጠይቁ ቆይተዋል
ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ጨምሮ ሁለት ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀቁ፡፡
የኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ክልሎች አራት ኪሎ በሚገኘው ቢሮው አካባቢ እንዳሰሩት የስራ ባልደረባው እና ባለቤቱ በወቅቱ ተናግረው ነበር።
ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴድሮስ ዘርፉ በተመሳሳይ ለእስር ተዳርጎ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከእስር ሲለቀቅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ደግሞ ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉን ጠበቃቸው ታለማ ግዛቸው እና የስራ ባልደረባው በለጠ ካሳ ለአል ዐይን አረጋግጠዋል፡፡
እንደ ጠበቃ ታለማ አስተያየት ጋዜጠኞቹ በአፋር ክልል በሚገኘው አዋሽ አርባ እስር ቤት እና በአዲስ አበባ ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው ቆይተዋል፡፡
ጋዜጠኞቹ ከእስር የተለቀቁት እንዴት ነው? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄም “ፌደራል ፖሊስ ጋዜጠኞቹን ያለ ዋስትና ከእስር ለቋቸዋል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ፣ ቴድሮስ ወርቁ፣ በቃሉ አላምረው እና ሀሊማ አህመድን ከእስር ለማስፈታት በፌደራል ፖሊስ ላይ አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መመስረታቸውን የሚናገሩት ጠበቃ ታለማ ጉዳዩ በልደታ ፍርድ ቤት ለነገ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
ከእስር እንዲለቀቁ አካልን ነጻ የማውጣት ክስ ከተመሰረተላቸው መካከል ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ቴድሮስ ዘርፉ ከቀጠሮው በፊት ከእስር ሲፈቱ በሀሊማ አህመድ ላይ ክስ እንደተመሰረተባትም ጠበቃ ታለማ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ ጠየቀ
የኢትዮጵያ መንግስት በፈጸማቸው የድሮን ጥቃቶች 248 ንጹሃን ተገድለዋል - ተመድ
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ለምን ከእስር አልተፈታም በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ምክንያቱን እስካሁን እንደማያውቁ ክስም እንዳልተመሰረተበት ተናግረዋል፡፡
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጂ ባሳለፍነው ታህሳስ ባወጣው ሪፖርት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ጨምሮ ሌሎች ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቆ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰማኮ) በበኩሉ በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩ ዜጎች ሁሉ ከእስር እንዲለቀቁ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡