ሩሲያ በዩክሬን ላይ በ110 ድሮኖች በፈጸመችው ጥቃት ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን አወደመች
ዩክሬንም በድሮን ጥቀት የፈጸመች ሲሆን፤ የሩሲያ የአየር መከላከያ 15 የዩክሬን ድሮኖችን መትቶ ጥሏል
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በ1 ሺህ 13ኛ ቀኑ ምን አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዷል?
የሩሲያ ክሬን ጦርነት ከተጀመረ 1 ሺህ 13ኛ ቀኑን ዛሬ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ካሳለፈነው ሳምንት ወዲህ ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋሩ እየተነገረ ይገኛል።
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም በምድር እና በአየር ላይ ውጊያ የቀጠለ ሲሆን፤ ሁለቱም ሀገራት ከሚሳዔል በተጨማሪ በድሮን የሚፈጽሙት ጥቃትም ተባብሶ ቀጥሏል።
ሩሲያ አዳሩን በዩክሬን የተለያዩ ግዛቶች ላይ በ110 ድሮኖች ጥቃት በፈጸሟን እና ከሩሲያ ድሮኖች ውስጥ 52 መትቶ መጣሉን እንዲሁም ከ50 በላይ ድሮኖች መከላከያውን በማለፍ ጉዳት ማድረሳቸውን ዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
- ሩሲያ የዩክሬን ከተሞችን በክሩዝ ሚሳዔሎች ደበደበች
- ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች ነው ተባለ
- ዩክሬን በኩርስክ ግዛት ከተቆጣጠረቻቸው ቦታዎች ውስጥ 40 በመቶውን በሩሲያ መነጠቋን አመነች
የሩሲያ ድሮኖች በዩክሬን ቴርኖፒል እና ሪቭን ክልሎች የሚገኙ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ማውደማቸውም ነው የተገለጸው።
መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ባደረገው የሩሲያ የድሮን ጥቃት ቴርኖፒል ከተማን በከፊል ከአሌክትሪክ ኃይል ውጪ ማደረጉም ነው የተገለጸው።
ዩክሬንም አዳሩን በሩሲያ ላይ በድሮን ጥቃት መፈጸሟ የተነገረ ሲሆን፤ ከዩክሬን ድሮኖች ውስጥ 15 በሩሲያ የአየር መከላከያ ተመትው መውደቃቸውን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል።
ዩክሬን በትናንትናው እለት በሩሲያዋ ምእራብ ብሪያንስክ ክልል በድሮን በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ህጻን ልጅ ህይወት ማለፉን የክልሉ አስተዳዳሪ አሌክሳንደር ቦጎማዝ መናገራው ይታወሳል።
በምድር ላይ እየተደረገ ባለው ውጊያም የሩሲያ ጦር ወደፊት የሚያደርገውን ግስጋሴ እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገጠመችው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።
የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 235 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት ተቆጣጥሯል የተባለ ሲሆን፤ ይህም የፈረንጆቹ 2024 አዲስ ክብረወሰን ነው።
ሩሲያ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ህዳር ወር ብቻ 600 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት መቆጣጠሯንም ዲፕ ስቴት የተባለውን እና ለዩክሬን ጦር ቅርበት ያለውን ተቋም ዋቢ በማድረግም የወጣ መረጃ ያመለክታል።