
የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ “የእግድ ውሳኔው በግል የተወሰደ፤ ተቋማዊ አሰራርንና ህግን ያልተከተለ ነው” ብሏል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሶስት የትግራይ ሠራዊት አዛዦችን ማገዳቸውን አስታውቀዋል።
በትናንትው እለት የአቶ ጌታቸው ረዳ የተጻፈ ደብዳቤ ሶስት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ማለትም፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በግዜያዊነት መታገዳቸውን ያመለክታል።
መጋት 1 ቀን 2017 ዓ.ም የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ ሶስቱ ከፍተኛ ወታራዊ አመራሮች በጊዜያዊነት የታገዱት ከመግስት እውቅና እና ውሳኔ ውጪ የክልሉን ህዝብ ወደ ችግር፣ ወጣቱን ወደ አመጽ እና የጸጥታ ሀይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ብሏል።
ጊዜያው አስተዳሩ በድበዳበው ላይ የከፍተኛ ወታራዊ አመራቹ እንቅስቀሴ “ህዝቡ ወደማይወጣው አዘቅት የሚከት ነው” ሲልም ገልጿል።
አሁን ያለው ችግር ህጋዊ በሆነ መንገድ ስምምነት እስኪቀረፍ ድረስ ከፍተኛ ወታራዊ አመራሮቹ ታግደው እንደሚቆዩም ነው ደብዳቤው ያመለከተው።
ለከፍተኛ ወታራዊ አመራሮቹ የተጻፈው የእግድ ደብዳቤ ላይ በግልባጭ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ እንዲሁም የትግራይ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲያውቀት መደረጉም ተመላክቷል።
በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫው “የእግድ ውሳኔው ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” በማለት እንደማይቀበለው አስታውቋል።
የእግድ እርምጃውን “በግል የተወሰደ እና ያልሾመውን ያወረደ ነው” ያለው ቢሮው፤ “የእግዱ እርምጃ የተላለፈው በወንጀለኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ስለተጀመረ ነው” ብሏል።
ቢሮው “የወንጀለኞች ጠበቃ መሆን ይብቃ” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫው ስልጣንን ተጠቅሞ ወንጀልን እና ወንጀለኞችን ለመከላከም እና ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ሊቆም ይገባል” ሲል አሳስቧል።
በደብረጺን ገብረሚካዔል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓትም በሶስት የትግራይ ሰራዊት አዛዦች ላይ የተላለፈውን እግድ “የማይተገበር ነው” ሲል ውድቅ አድርጎታል።
በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ህወሓት ሌሊት በማበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫው፤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን ማንሳቱን በማስታወስ፤ እገዳውን “እጃቸው ላይ በሌለ ስልጣን የወሰዱት እርምጃ ነው” በማለት አጣጥሎታል።
“እገዳው የማይተበር እና መሰረተ ቢስ ነው” ያለው በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ህወሓት "እርምጃው የትግይ ሰራዊትን ለማፍረስ ሲደረግ የቆየው ተንኮል አካል ነው ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት ሲልም ጥሪ አስተላፏል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ በሚመራው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር እና በዶ/ር ደብረጺዮን መካከል ካሳለፍነው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ ይገኛል።
በእነ ደብረፅዮን ገበረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ “አቶ ጌታቸው ረዳን ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትነት አንስቻለሁ” ማለቱም ይታወሳል።
ፓርቲው አቶ ጌታቸውን እንዴትና በማን እንደሚተኩ ከፌዴራል መንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ይወሰናል ሲል መግለጹም አይዘነጋም።
“ይህን ተከትሎ አቶ ጌታቸው በሚመሩት የህወሓት ቡድን የሚመራው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድን ይፋዊ መፈንቅለ መንግስት አውጆብኛል ሲል ከሷል።
የሁለቱ ቡድኖች አለመግባባት ወደ ግጭት እንዳይገባ የትግራይ የጸጥታ ኃይል እጁን እንዳያስገባ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።