ይፋ የተደረጉት በክልሉ ከሚያስፈልጉት 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ ጀምረዋል ተብሏል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡
በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ …… የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ …… የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ …… የጤና ቢሮ ሃላፊ
አቶ አበራ ንጉሴ ………. የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ……… የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
አቶ ዮሴፍ ተስፋይ ………. የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን …….. የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ ……. የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ
አቶ ሰለሞን አበራ …….. የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ
አቶ አብርሃ ደስታ ……. የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ እና አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡
ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡