ፖለቲካ
ሁለት የተመድ ቡድኖች ትናንት ትግራይ ገብተዋል
ያልተቆራረጡ ሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲኖሩ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ሊያዳርሱ እንደሚገባም ኮሚሽኑ አሳስቧል
ቡድኖቹ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ ናቸው ተብሏል
በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ ሁለት ቡድኖቹ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ቡድኖቹ ትናንት ሰኞ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የገለጹት የኮሚሽኑ ሃላፊ ሚሼል ባሸሌት የኢትዮጵያ መንግስት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ያልተቆራረጡ ሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲኖሩ መፍቀዱን መቀበላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሆኖም ሰብዓዊ አቅርቦቶቹ በጦርነቱ የተጎዱ ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ሊያዳርሱ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡
ባሸሌት ከዓለም አቀፍ ህግጋት በተጣረሰ መልኩ በተሰባሰበ ህዝብ ላይ የመተኮስ፣ ሆን ብሎ ንጹሃንን ዒላማ የማድረግ፣ የግድያ እና ዝርፊያ ድርጊቶች ጭምር እንዳሉ የሚያለክቱ መረጃዎች ደርሰውናል ብለዋል፡፡
ይህ ሁለቱም ወገኖች ንጹሃንን ለመጠበቅ አለቻላቸውን የሚያሳይ ነው ያሉም ሲሆን ጦርነቱ በክልሉ ሰሜናዊ፣ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ አካባቢዎች ቀጥሏል መባሉ ይበልጥ እንዳሳሰባቸውም ነው ኮሚሽነሯ የገለጹት፡፡