በየመን በ2022 ብቻ 1 ሺህ 500 ቶን ማር መመረቱን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያሳያል
የመናዊው አብዱልጀባር አል ጎሊ በጦርነት በደቀቀችው ሀገሩ ከንቦች ጋር ይውላል።
የስምንት አመቱ ጦርነት ገበያውን ቢያቀዘቅዘውም ለንቦችና ለማር ያለው ፍቅር እየጨመረ መሄዱን ይናገራል።
“ለንቦች ፍቅሬን ለመግለጽ ፊቴ እና ሰውነቴን እንዲወሩኝ አደርጋለሁ” የሚለው አብዱልጀባር፥ ንቦችን በብልሃት መያዝ እንደሚገባ ያነሳል።
እርሱ ግን ባህሪያቸውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እንደማይነድፉትና አንዳንዴ ቢገጥመው እንኳን “እንደ መሳም” እንደሚቆጥረው ለሬውተርስ ተናግሯል።
እንደ መንግስታቱ ድርጅት መረጃ በየመን ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በማር ምርት የሚተዳደሩ ሲሆን፥ ባለፈው አመት ብቻ ከ1 ሺህ 500 ቶን በላይ ማር ተመርቷል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic