በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 789 ሺህ ደረሰ
በአጠቃላይ በአማራ ክልል 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተፈናቃይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙም ነው የተገለጸው
በህወሓት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል ለመድረስ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 789 ሺህ ደረሰ።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለአል ዐይን አማርኛ እንደገለጸው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት 789 ሺህ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።
በአማራ ክልል አራት ሚሊዬን ዜጎች ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
በተቋሙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ጀምበሩ ደሴ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት ህወሓት በአማራ ክልል አምስት ዞኖች ማለትም በሰሜን ወሎ፣በዋግ ኸምራ፣በደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ጥቃት ከፍቶ በርካታ ንጹሀንን አፈናቅሏል።
በአጠቃላይ በአማራ ክልል 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተፈናቃይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 789 ሺህ ያህሉ ህወሓት በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ናቸው ብለዋል አቶ ጀምበሩ።
ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያ፣ ከትግራይ፣ ከአፋር፣ ከጅቡቲ እና በክልሉ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ መሆናቸውንም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
አቶ ጀምበሩ የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው ድጋፍ በመጠለያ ጣቢያዎች ላሉ ተፈናቃይ ዜጎች ለአንድ ወር የሚበቃ ምግብ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
በአፋር ክልል ህወሓት በፈጸመው ጥቃት 107 ህጻናትን ጨምሮ 240 ተፋናቃዮች መግደሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ
ህወሓት በዋግ ኸምራ ዞን በከፈተው ጥቃት መኖሪያ ቤቱን ለቆ በባህርዳር ተጠልሎ ያለ እና ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ አንድ ተፈናቃይ ለአል ዐይን አማርኛ እንደገለጸው ከሆነ ግን በመጠለያ ጣቢያው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
የዕለት ደራሽ ምግብ ከመንግስት ተቋማት እና ገብረሰናይ ድርጅቶች ይልቅ ከአካባቢው ማህበረሰብ እያገኙና ማህበረሰቡ የተሻለ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነም ነው ተፈናቃዩ የተናገረው፡፡
በተለይም ስኳርን መሰል ሌሎች ቋሚ ህመም ያለባቸው ጽኑ ታማሚዎች የመድሀኒት እጥረት አጋጥሟቸው ህይወታቸው አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል የሚልም ሲሆን በቅርቡ የወለዱ እናቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ችግር የከፋ መሆኑንም አክሏል።
ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ የከፋ የምግብ ችግር እንደሌለባቸው የገለጹት አቶ ጀምበሩም ይህን አልሸሸጉም፡፡ የአልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ችግር አለብንም ብለዋል፡፡
በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ባሉ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፎችን በቀጥታ ለማድረስ አለመቻሉን የገለጹም ሲሆን በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በውይይት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
በአማራና በአፋር ክልሎች ከ1 ሺህ 400 በላይ የጤና ተቋማት መጎዳታቸውን የጤና ሚንስቴር አስታወቀ
ከቅርብ ወራት ወዲህ ከትግራይ ወደ አማራ ክልል አካባቢዎች ተዛምቶ አምስቱን የዞን መስተዳድሮች ያዳረሰው ጦርነት ህወሓት የሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ነው በይፋ የተጀመረው፡፡
አፋጣኝ የአጸፋ እርምጃዎችን እንዲወስድ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተሰጠው የሃገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ጨምሮ ዋና ዋና በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓትን ጠንካራ ይዞታዎች በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር ቢችልም መንግስት ባሳለፍነው ወርሃ ሰኔ ላይ የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ ክልሉን ለቆ ወጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎም ነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሓት የአማራ እና አፋር ክልሎችን ከመውረር ባለፈ ጥቃቶችን የፈጸመው፡፡
ህወሓት ኃይሎቹን በአስቸኳይ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲያስወጣ አሜሪካ አሳሰበች
በጥቃቶቹ በርካታ ንጹሃን ተገድለዋል፤ ተፈናቅለዋል መሰረተ ልማቶችም ወድመዋል፡፡