በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ “ህወሓትን መታደግ” በሚል ስበሰባ እየተካሄደ ነው
በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ቡድን አቶ ጌታቸውን ጨምሮ በድርጅታዊ ጉባኤ አንሳተፍም ያሉ አባላቶችን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አንስቷል

አቶ ጌታቸው “በህወሓት ከፍተኛ አመራር ድክመት የተነሳ በሰራዊታችን የተገኘውን ወርቃማ ድል ተደናቅፏል” ብለዋል
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ መንብር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ “ህወሓትን መታደግ” በሚል በመቀሌ ከተማ ስበሰባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በስበሰባው ላይ ህወሓት በመደበኛ ጉባዔው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አንስቻቸዋለሁ ያለው አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
- ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኝው ህወሓት እነ ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አነሳ
- “ህወሓት በማካሄድ ላይ የሚገኝው ጉባኤ ትግራይንና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም” - አቶ ጌታቸው ረዳ
“ስበሰባው እየተካሄዱ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ ነው” ሲሉ የትግራይ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሀለፎ መናገራቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በስበሰባው ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ “በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ድክመት በሰራዊታችን የተገኘውን ወርቃማ ድል ተደናቅፏል” ብለዋል።
አሁን ያለው የፓርቲ አመራር አመራር “ችግሮቹን ተቀብሎ ፓርቲውን ለትውልድ የሚያስተላልፍ ሃይል አይደለም” ሲሉም ተናግረዋል።
“ልዩነቶቹ በውስጣችን ችግር ፈጥረው ጠላቶቻችን ሊጠቀሙባቸው የሚችሉበትን እድል ይፈጥራል” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የፖለቲካ አስተዳደር ድክመትም ሌላው ችግር መሆኑንም ተናግረዋል።
ህወሓት ድርጅታዊ ጉባዔ ጋር በተያያዘም “ከህወሓ ከፍተኛ አመራች ጋር የነበረው ትልቁ ልዩነት ኮንፈረንሱ መካሄዱ ሳይሆን እንዴት እንደተካሄደ ነው የሚለው እደሆነም” ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ፤ “ህወሓት ለማዳንና የትግራይ ሁኔታ ወደ ነበረበት ለመመለስ ይሄ መድረክ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን እያካሄደ ባለው ጉባኤ የፓርቲው ም/ሊቀመንብር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የሚሆኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በማገድ በተራ አባልነት ከመቀጠል ውጪ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም ማቱ ይታወሳል።
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ" የተለየ ሃሳብ አለኝ "የሚል በጉባኤ ያልተገኘ አካል ወደ ጉባኤው ቀርቦ ሃሳቡን በነፃነት እንዲገልፅ ፣ በዴሞክራሲያዊ ሙግት ለሚተላለፉት ውሳኔዎች ተገዢ" እንዲሆን ነሃሴ 8/2016 ዓ.ም ጥሪ ማቅረቡን አስታውሷል።
በዚህም የድርጅቱ ጉባኤ ከተሰየመበትና ከተጀመረበት ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ቀን በኋላ ያልተሳተፉ አመራሮች የተራ አባል እንጂ የማእከላዊ ኮሚቴ የሚባል ሃላፊነት የላቸውም ብሏል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ሊቀ መንብር አቶ ጌታቸው ረዳ በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ቡድ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፤ ውሳኔውን ተከትሎ “የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥልጣን ለመንጠቅ ሙከራ ሊደርግ ይችላል” ብለዋል።
አቶ ጌታው ኪህ ቀደም ጉባዔውን ስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ “ፓርቲውማካሄድ የጀመረው ጠቅላላ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም” ማለታቸው ይታወሳል።
ህወሓትምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ሲደርሱት የነበሩትን ማስጠንቀቂያዎችን ወደ ጎን በመተተው "የመዳን ጉባኤ" ሲል የሰየመውን 14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን፤ በዛሬው እለት ውሳኔዎችን በማሳለፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።