ሆነ ተብለው የተፈጸሙትን ሳይጨምር በጦርነቱ በአማራ እና አፋር ክልሎች 403 ንጹሀን መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
የጦርነቱ ተዋናዮች በወሰዱት የኃይል እርምጃ በርካታ ህጻናት መገደላቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል
በዋናነት የትግራይ ኃይሎች ቢያንስ 346 ሲቪል ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ መግደላቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል
የትግራይ ሀይሎች በአማራ እና አፋር ክልሎች 346 ንጹህን ሰዎችን ከዳኝነት ውጪ መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
ኢሰመኮ በህገ ወጥ መንገድ ከተገደሉት በተጨማሪ 309 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋልም ብሏል።
ግድያው በትግራይ ሀይሎች እና በመከላከያ መካከል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት የተፈጸመ ነው።
ኮሚሽኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ዛሬ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ይፋ አድርጓል፡፡
የትግራይ ግጭት ተሳታፊዎች “በተለያየ መጠን” የሰብአዊ መብቶችን መጣሳቸውን የምርመራ ቡድኑ ገለፀ
በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ እና አፋር ክልሎች በተካሄደው ጦርነት ላይ በተሳተፉ ሀይሎች 403 ንጹሀን ዜጎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ በምርመራው ሪፖርቱ ገልጿል።
እንዲሁም እነዚህ የጦርነቱ ተሳታፊዎች ከተገደሉት በተጨማሪ 309 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውም ነው ያስታወቀው።
የትግራይ ሀይሎች ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀልን እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀልን ሊያቋቁም በሚችል መልኩ የእገታ እና አስገድዶ መሰወር ተግባራትን እንደፈጸሙ የኢሰመኮ ሪፖርት ያስረዳል።
የፌደራል፣የአማራ እና አፋር ክልል የጸጥታ ሀይሎች መጠነ ሰፊ የዘፈቀደ እስር እንደፈጸሙም በሪፖርቱ ተገልጿል።
የህወሀት ሀይሎች በሁለቱ ክልሎች 346 ንጹሀንን ከህግ ወይም ከዳኝነት ውጪ በህገወጥ መንገድ መግደላቸውንም ነው ሪፖርቱ የሚያትተው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በምርመራ ሪፖርቱ የተወሰኑ ይዘቶች ላይ ትልቅ ቅሬታ እንዳለው ገለጸ
በሰዎች ላይ ከተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶ በተጨማሪ የግለሰቦች ንብረት፣ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት እና የግል ተቋማት በህወሀት ሀይሎች መዘረፋቸውና መውደማቸውም ተገልጿል።
ለአብነትም በአማራ ክልል 40 ሆስፒታሎች፣ 453 የጤና ተቋማት፣ 1850 የጤና ኬላዎች በድምሩ በአማራ ክልል ብቻ 2343 የጤና ተቋማት ፣ በአፋር ክልል ደግሞ በድምሩ 66 የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።
እንዲሁም በአማራ ክልል 1025 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ 3082 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሙሉ በከፊል ወድመዋል።
346 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆኑ ቅርንጫፎች ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በትግራይ ኃይሎች መዘረፉንም ገልጿል፡፡
በግጭቱ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ እንዳይቋቋሙ፣ ቶሎ እንዳያገግሙ እና ጥገኛ እንዲሆኑ መደረጉንም ኢሰመኮ አስታውቋል።
የማይካድራው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን የተገደሉበት ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ
የጤና መሰረተ ልማቶች በመውደማቸው በርካታ ነፍሰ ጡር እናቶች ህይወታቸው እንዳለፈም ተገልጿል። ለማሳያነትም በአማራ ክልል መቄት ወረዳ ብቻ 8 ነፍሰ ጡር እናቶች በዚሁ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉም ተገልጿል በሪፖርቱ፡፡
ኮሚሽኑ ሪፖርቱን በሁለቱ ክልሎች ባሉ 8 ዞኖች ተዘዋውሮ 427 ሚስጢራዊ ቃለመጠይቆችን፣ 136 ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት አመራሮች ጋር ስብሰባ ማድረጉን እና 12 የቡድን ውይይቶችን በማድረግ ሪፖርቱን እንዳጠናቀረ አስታውቋል።